ቲፒልፈ ኣሰብ ለኢትዮጵያ ኣያስፈልግም በሚል ጥኑ ተቃውሞ ምክንያት ኢትዮጵያ ኣሰብን ያጣችበት ሚስጢር የበለጠ ግልጽ ሆነ
ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው። ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150
ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። ይህ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ወደ
30 ገጽ የሚሆን ተባዝቶ በመጽሓፍ መልክ ተጠርዞ በብዛት ተያዘ። በሃላፊነት የጻፉት አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ ናቸው። በየቦታው እንዲሰራጭም ተደረገ። ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ኢትዮጵያን ለመበታተን፣ ሕዝቧን በዘርና በጎሳ የከፋፈለ፣ አማራውን ደመኛ ጠላት ብሎ ያወገዘ ሆኖ የመጣና እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የሆነ አስተሳሰብ ነበር። በአርከበ እቁባይ የተዘጋጀ ካርታ ከበጌምድር ጠ/ግዛት ከላይ የተጠቀሱትን ቦታዎ ች፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ራያና ቆቦ፣ አላማጣ፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ ለምትመሰረተው አዲሲቷ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትግራይ ሲካተቱ፣ በምእራብ በኩል ደግሞ ወልቃይት፣ ሁመራ ፀለምት፣ ፀገዴ ተጨምረው ትግራይ ከሱዳን ጠረፍ ጋር እንደትገናኝ፣ በደቡብ በኩል ደግሞ ወደውሃ ምላሽ ትግራይ እንድትሰፋ ሲወስን፣ እነዚህ ቦታዎች ሁሉ ለምና ሃብታም መሬቶች ናቸው። ይህንን ውጥን ለማሳካት በወልቃይት ፀገዴ ተሓህት ህዝቡን እያፈነ ማጥቃት ጀመረ። የወያኔ/ህወሓት/ተሓህት መሰረታዊ የታሪክ ወንጀል የወላቅይት ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ ለብዙ ሺህ ዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ታሪካዊ ቦታዎች የበጌምድር (ጎንደር) ግዛት መሬት ነው። በወልቃይት ፀገዴ ጥቃቱን ያቀነባበሩት አመራሮች፤ ስየ አብርሃ፤ አርከበ እቁባይ፤ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤ አውአሎም ወልዱ ናቸው። እነዚህ በሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት ፀገዴ ትእዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ሲሆኑ፤ ይህንን ሁሉ በበላይነት የመራው ስብሃት ነጋ ሲሆን፤ የቅርብ ተባባሪዎቹ ደግሞ አባይ ፀሃየና አርከበ እቁባይ ነበሩ። ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር የሰሜን ጎንደር ኗሪ ሰላማዊ ህዝብ ለማጥቃት የታየው ሁኔታ አመራሩ ዝግጅት ያደረገው ነበር።
እነዚህ ከበጌምድር ጠ/ግዛት በተሓህት/ህወሓት የተነጠቁት መሬቶች፣ ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ደግሞ ደቡብ ወሎ የተነጠቁት ቦታዎች ሕገወጥ ናቸው። ተስፋፊው ተሓህት በፕሮግራሙ መቅድም በሚለው አርእስት ያካተተው የትግራይ ቦታዎች ናቸው የሚለው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያው፣ ከ1969
ጀምሮ በቁርጠኝነት የተቃወመው ነው። ወያኔ ህወሓት ወደ ሰሜን በጌምድር ሲዘምት ዋናው አስተባባሪ ሆኖ እልቂቱ እንዲፈጸም ያስተባበረው የድርጅቱ ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ነበር። ከስብሃት ነጋ ጋር በመተባባር በተግባር የዘር እልቂት እንዲፈጽሙ የተመደቡት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ፣ አርከበ እቁባይ፣ ስዩም መስፈን፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ስየ አብርሃ ናቸው። በእልቂቱ የታሰተፉ ተዋጊ ሃይሎች የተመሩት ደግሞ፣ በሳሞራ የኑስ፣ ተከስተ እስጢፋኖስ፣ ታደሰ ወረደ፣ መኮንን አሊሱም ሲሆኑ፤ ክርቢት ተብለው የሚታወቁት ሽብርተኛ ጋንታ የተመሩት ደግሞ፤ በሻሸይ በላይ፣ አሰፋ ማሞ፣ ጸጋይ ቆማጥ፣ መሃሪ፣ ዳሳ ጉግሳ ነበሩ። አምስተኛ ክርቢት ደግሞ የተመራው በአርከበ እቁባይ ሲሆን፣ ስምሪታቸው በፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ፀለምት ነበር። እዚህ የሚኖረው ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ነው። እኛ በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን አማሮች ነን በማለታቸው፣ በቀንና በሌሊት እሳተ ነበልባል ወረደባቸው። በስብሃት ነጋ በሚመራው የህወሓት ሰራዊት ከያሉበት እየተለቀሙ በጥይት እየተደበደቡ አለቁ። ሃብት ንብረታቸው፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ የጋማ ከብት፣ ያፈሩት ንብረት ሁሉ በህወሓት እየተዘረፈ ወደ ትግራይ እየመጣ የሰራዊቱ ቀለብ ሆነ። ቤት ፈረሰ፣ ወላጆች፣ ህፃናትን ጨመሮ በህወሓት አለቁ። ቤተሰቦች እየተሰበሰቡ እቤት ወስጥ እየታጎሩ አርከበ እቁባይ በሚመራው ክርቢት እሳት እየተለቀቀባቸው በእሳት አጋይተው ጨረሷቸው። ወያኔ ኣኢትዮጵያ ከተቆጣጠረ በ ሁ ኣላ ኣሳብ ለ ኣኢትዮጵያ እንዳይሆን ኣደራዳሪዎችንም ሆነ ሻቢያን ተቃወመ ተንታኞች እንደሚሉት ጠላት ብሎ የፈረጀው ህዝብ በቅርብ እርቀት የባህር ወደብ ያገኛል ብሎ ስለ ኣሰበ ነው ሁለተኛው ታላቂቷ ትግራይ የጎንድርን መሬት በመቀማት ከሱጽዳን ጋር ስለተገናኘች ሌሎች በተለይ ኣማራው ከውጭ ኣገራት ጋር ለመገናኘት የትግራይ ጥገኛ ለማድረግ ነው በ ኣጠቃላይ ከሱዳን ጋር በመሻረክ ኣፍኖ ለመግዛት ከነበረው መርዛማ እቅድ የመነጨ ነው በተጨማሪ ህዋሃት በ ጋምብቤላ ኣኡጋዴን ኣኦሮም ያ ሲዳማ ኣፍር እና ሌሎች ላይ የፈጸመውን ደባ ኣጋልጠዋል በመጨርሻም ብቸኛው መፍትሔ ወያኔን በትብብር ማስወገድ ነው ሲሉ ኣስረድተዋለ
No comments:
Post a Comment