Tuesday, December 15, 2015

ከወያኔ ደህንነት ቢሮ ያፈተለከ መረጃ ለሰፊዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በሙሉ



ህወሃት ሰሞኑን በተለያዩ የሃገሪቱ ቦታዎች በተነሳዉ አመጽ የተነሳ የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ አጥቷል፡፡ስለሆነም የተነሳዉን ህዝባዊ ማዕበል ለመቀልበስ እና የአመጹን ትኩረት ለማስቀየስ ፕሮፖዛል ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ከደህንነት ቢሮ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ከነዚህም ዉስጥ፡-
1.በፌስ ቡክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያዩ የአማራና የኦሮሞ ስሞች በመጠቀም ስሜታዊ የሆኑ ጽኁፎችን በመልቀቅ አማራዉንና ኦሮሞዉን ማጋጨት፤
2.በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በመተንኮስ አማራዉን እና ኦሮሞዉን ማጋጨት
3.በወቅቱ በነበሩ ገዥዎች በተፈጸመ የድሮ ቁርሾን በማንሳት የኦሮሞን ህዝብ ስሜታዊ ማድረግና በገዥዎች አብሮ ሲጨቆን ከነበረዉ የአማራ ህዝብ ጋር ማጋጨትና ህብረታቸዉን መስበር የሚሉት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡
ይህንን ዕቅድ ለማስፈፀምም አማራዉን ስሜታዊ የሚያደርጉ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ የህወሃት ተላላኪ ትግሬዎችን አደራጅቷል፡፡እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብን ለማበሳጨትና ስሜታዊ ለማድረግ በአማራ ስም የሚነግዱ የህወሃት ተላላኪ ትግሬዎችን እንዳደራጀ ሰምተናል፡፡ የተከበርከዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ሆይ አማራና ኦሮሞ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋትም ሆነ በህዝብ ብዛት የሃገሪቱን 80ፐርሰንት እንደሚወክል ይታወቃል ፡፡በጣም የሚገርመዉ ግን እነዚህን ህዝቦች የሚያስተዳድራቸዉ ከራሳቸዉ የወጣ ሳይሆን የሃገሪቱን 4ፐርሰንት የህዘብ ብዛትና የቆዳ ስፋት የማሸፍኑት አናሳ ትግሬዎች ናቸዉ፡፡
የኦሮሞ ና የአማራዉ ህዝብ አንድነት ምን ያህል ለህወሃት የራስ ምታት መሆኑንና ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣቱ እሁድ 03/04/08ዓ.ም በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ራዲዮ ጣቢያ ብሩክ ከበደ በሚያዘጋጀዉ ሞጋች ፕሮግራም የቀረበዉ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በተደጋጋሚ በወያኔ አባባል የትምክት ሀይሉ(አማራዉ)ና የጥበት ሀይሉ(ኦሮሞዉ)በአንድ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረዉን የሰማ ሰዉ ምን ያህል የነዚህ ህዝቦች ጥምረት ህወሃትን እንቅልፍ እንደነሳዉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለዚህ እነዚህ አናሳዎች ስልጣናቸዉን ለማራዘም የቀየሱትን ሴራ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ተባብሮ ሊያመክነዉ ይገባል፡፡የአማራ ህዝብም ሆነ የኦሮሞ ህዝብ ልንረዳዉ የሚገባን ጠላታችን አንድና አንድ ነዉ እርሱም በሰፊዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ደም የሚቀልደዉ የአናሳ ህዝብ ተወካይ የሆነዉ ህወሃት ነዉ፡፡ስለሆነም የአማራና የኦሮሞ ህዘብ በመካከሉ እንኳን ልዩነት ካለ ከነጻነት በኃላ ተወያይተን የምንፈተዉ ጉዳይ ሲሆን አሁን ባላዉ ተጨባጭ ሁኔታ የአማራዉና የኦሮሞዉ ቅራኔ በሀገሪቱ የተቀጣጠለዉን አብዮት ዉሃ ከመቸለስ ዉጭ ምንም እርባና የለዉም፡፡ስለዚህ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ በአንድነት በመነሳት ጠላታችንን ድል የምንነሳበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን፡፡
ያለመሰዋትነት ነጻነት አይገኝም!!!ድል ለሰፊዉ ህዝብ!!!

No comments:

Post a Comment