Monday, September 7, 2015

አትሌቱ እስካሁን የት እንዳለ አይታወቅም

 የዓረና ትግራይ ደጋፊ ነበር ወያኔ ዓረናዎችን በጣም ነው የሚፈራቸው በማራቶን ሩጫ አገራችንን ካስጠሩት ወጣት አትሌቶች አንዱ አብርሃ አማረ በቅርቡ ለውድድር ወደ ካናዳ ከተጓዘ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱና አለመመለሱ አልታወቀም። በአዲስ አበባ ያለው የልሳነ ህዝብ ዘገጋቢ እንደገለፀው አብርሃ የዓረና ትግራይ ደጋፊ እንደነበርና በዚሁ ምክንያትም በአዲስ አበባ ከተማ የሰራው የግል ቤቱ በመንግስት ሰዎች ካለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ተቀምቶ ለአንድ የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣን ስንደተሰጠ ለማረራገጥ ችሏል። አብርሃ በዚሁ ፖለቲካ ተሳትፎወ ምክንያት በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበረና ከእስር ቤት ከወጣ በሁዋላ ደስተኛ እንዳልነበር ከቅርብ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አብርሃ ሙሉ እራሱ የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ ምክንያት ዓረና ትግራይን መደገፉ ከማንኛውም ተቃዋሚ በላይ ወያኔዎችን እንደሚያናድዳቸው ይታወቃል። አትሌት አብርሃ ሙሉ በበርካታ ኢንተርናሽናል ውድድሮች የአገራችንን ባንዲራ አንግቦ ለክብራችን የሮጠ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በ2008 በቫሌንሺያ ፣ በ2009 ፖላንድ ዋርሶውና በሳን አንቶንዮ አሜሪካ፣ 2011 በግራን ካናሪያ ስፔንና በ2011 ሉብጂ ሉብጃና 1ኛ በመውጣት በሁለቱም አገሮች የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል። በ2014 በቻይና ተወዳድሯል። በመጨረሻ በ2015 በቶሮንቶ ካናዳ ከወዳደረና ውድድሩን በ2ኛነት ከካጠናቀቀ በሁዋላ ወዴት እንደገባ ሳይታወቅ ቀርቷል። አንዳንድ ሰዎች አትሌቱ ከመንግስት ጋር ከነበረው ግጭት በመነሳት ምናልባት ወደዳገር ቤት ተመልሶ በወያኔ ደህንነቶች ታፍኖ ሊሆን ይችላል ሲሉ አንዳንዱ ደግሞ ምናልባት ወዳገር ቤት ሳይመለስ ቀርቶ ይሆናል ይላሉ። ወያኔ እንደ የዓረና ትግራይ ደጋፊና አባላት የሚያስፈሩት ያህል ምንም ነገር አያስፈራውም፡፡ ወያኔ ሙሉ በሙሉ ይደግፈኛል እያለ የሚመካበት የትግራይ ህዝብ እንደካደው ሲያውቅ በተጠርጣሪ የትግራይ ሰዎች ለይ የሚያደርሰው ቅጣት ከባድ ነው። ምናልባት አትሌት አብርሃ ሙሉንም መቀጣጫ ለማድረግ ሲል አፍኖት ሊሆን ይችላል። ስለ አትሌቱ ዕውቀት ያላችሁ ታዳሚዎቻችን lisanehizb@mail.com ላይ ኢሜይል እንድትልኩልን በትህትና እንጠይቃለን። አትሌታችን ሰላም እንዲሆንም እንመኝለታለን።  

No comments:

Post a Comment