
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
No comments:
Post a Comment