ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ
ምድር ስታጌጥ አድማስ ሲፈካ
ከሚገዳደር ያንቺን ሕላዌ
ዘገር ከሚሰብቅ ከክፉ ደዌ
ከዘውጌ ልምሻ ሥርየት አግኝተሽ
የፍትሕ ጸበል ቡራኬ ጠጥተሽ
በሕዝብሽ ኅብር ተውበሽ ፈክተሽ
በዓለት ላይ ቁሞ ያንድነት ካስማ
እናፍቃለሁ ደግ ነገር ላይ፣በጎ ልሰማ
ከፍ ብለሽ ላይሽ በክብር ማማ፤
የፈጠረቀሽ-ክፉ ፃረ ሞት-ራሱ ታንቆ
ሕያው እስትንፋስ ከከርስሽ ፈልቆ
ሥርየት ስታገኝ ህልም አልማለሁ
ጧቱ እንዲያምርልሽ ሰርክ እመኛለሁ፡፡
መጣሁ ሲል ዘመን-ልቤ ይጎናል-ተስፋ ያንቀኛል
ትንሣኤ አግኝተሽ-ክፉ ቀን አልፎ-ማየት ያምረኛል፡፡
ዘር ሳይዘራ-ሙቶ እንዲነሣ-ሳይኮተኮት ውኃ ሳይጠጣ
ከጥላቻ ሥር-ከጠብ አዝመራ-ማየት ያምረኛል መሲህ ሲወጣ
የሚያስከብርሽ-ውርደት ዝቅታን-አሻፈረኝ ባይ
ምድር ስታጌጥ አድማስ ሲፈካ
ከሚገዳደር ያንቺን ሕላዌ
ዘገር ከሚሰብቅ ከክፉ ደዌ
ከዘውጌ ልምሻ ሥርየት አግኝተሽ
የፍትሕ ጸበል ቡራኬ ጠጥተሽ
በሕዝብሽ ኅብር ተውበሽ ፈክተሽ
በዓለት ላይ ቁሞ ያንድነት ካስማ
እናፍቃለሁ ደግ ነገር ላይ፣በጎ ልሰማ
ከፍ ብለሽ ላይሽ በክብር ማማ፤
የፈጠረቀሽ-ክፉ ፃረ ሞት-ራሱ ታንቆ
ሕያው እስትንፋስ ከከርስሽ ፈልቆ
ሥርየት ስታገኝ ህልም አልማለሁ
ጧቱ እንዲያምርልሽ ሰርክ እመኛለሁ፡፡
መጣሁ ሲል ዘመን-ልቤ ይጎናል-ተስፋ ያንቀኛል
ትንሣኤ አግኝተሽ-ክፉ ቀን አልፎ-ማየት ያምረኛል፡፡
ዘር ሳይዘራ-ሙቶ እንዲነሣ-ሳይኮተኮት ውኃ ሳይጠጣ
ከጥላቻ ሥር-ከጠብ አዝመራ-ማየት ያምረኛል መሲህ ሲወጣ
የሚያስከብርሽ-ውርደት ዝቅታን-አሻፈረኝ ባይ
ጀግና ያምረኛል-ለሐቅ የሚሞት-ባንቺ ሰማይ ላይ፤
ከአሮጌው ጋራ ክፉን የሚሸኝ-ኅብርን የሚያዜም-ያንድነት አቡን
ኢትዮጵያን የሚል-መንገድ ጠራጊ-አርቆ ዓላሚ የሚበጀንን
ከአይመክኔ ማሕፀን-ከለሙ ማሳሽ-ከደጅሽ ፈልቆ
ውድቀትሽን ሽቶ-ጉድጓድ የማሰን-ጅስሙን አድቅቆ
ማየት ያምረኛል-ምድርሽ በፍትሕ-በሐቅ ደምቆ፡፡
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ
የአገሬ ጀምበር አምራ ስትፈካ
በማንነቱ ልጇ ሲመካ
ከሺሕ ዘመናት ታሪክ ደክታ
እመር ስትል ዘመኑን ዋጅታ
መጠጊያ ሁና የሕዝቧ ዋልታ
ስደት ቀርቶላት ቸነፈር አልፎ
የውርደት ካባ ወድቆ ተገፎ
ማየት እሻለሁ-በሞገስ ቁማ-ክብሯ ተሟልቶ
የተሰበቀው-የጠላት ደባ-ሴራው ተራቁቶ፡፡
ወንድወሰን ውቤ
ጳጉሜ 3/2007 ዓ.ም.
No comments:
Post a Comment