
ወጣት ሰሎሜ ጉልላት በሞራልም ሆነ በግብር ከወደቁና የስርኣቱን ዙፋን ለማስጠበቅ ተመልምለው መሳርያ ከታጠቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአንዱ በተከታታይ የጥይት ድብደባ ህይወቷ አልፏል። በነኝህ ሃይሎች ንፁሃን ዜጎቻችን (በተለይም ሴት እህቶቻችን) እንዲህ ላለው አደጋ ሲጋለጡ ይህ የመጀመርያ አይደለም። "የሴቶችን መብት አስከበርሁ" እያለ በሰርክ ፈሊጡ ፕሮፓጋንዳውን የሚነፋብን ይሄው ስርኣትም ሴቶች ላይ "ነፃ እርምጃ" በሚመስል አኩዋሃን ውድ ህይወታቸውን ያለስስት በአረመኔዎች እያስቀጠፈ ይገኛል። በታጠቁት መሳርያ የግል ቂማቸውን መወጫ ያደረጉ ጠባቂዎቹንም እንደተለመደው ሁሉ "እኛን አይወክሉም" በሚል ጥቅስ ሸፋፍኖ እንደሚያልፈውም የሚጠበቅ ነው። እኛ ግን እንላለን፦ ከሰማይም ይሁን ከምድር ፍትህ ለሰሎሜ!
ነፍስሽን በገነት ያኑር
ነፍስሽን በገነት ያኑር
No comments:
Post a Comment