Friday, October 30, 2015

አንድነት አንድነት አንድነት


ኢሳት አምስተኛ አመቱን አገባዶ ስድስተኛ አመቱን ጀምሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ አይን እና ጆሮ ሆኖ ከመቼውም በላይ መረጃዎችን በፍጥነት እያዳረስ ይገኛል።ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በኦስሎ ኖርዌይ የኢሳት አምስተኛ አመት ሲከበር በስፍራው ተገኝቶ በወኔ ያስተላለፈውን መልክት  ደጋግመው ቢሰሙት አይጠገብም አንድነት አንድነት አንድነት 

Tuesday, October 20, 2015

ጤና ይስጥልኝ ይህ የኢትዮ ኖርዌይ ቲቪ ሳምንታዊ የዜና ዘገባ ነው


በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ግጭት ተከስቷል
በቅርቡ የተከሰተው ግጭት ባሳለፍነው ወር ስምንት ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያን በሱዳን የመከላከያ ሰራዊት መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ከሆነ የአሁኑ ግጭት የተፈጠረው ባለፈው ወር የተገደሉባቸውን ወገኖቻቸውን ደም ለመበቀል ሱዳን ክልል ውስጥ ወደምትገኘው አትራድ ኢትዮጵያዊያኑ መሳሪያ ታጥቀው በመግታቸው ነው፡፡
ኦስካር ፒስቶሪየስ ይፈታል ተባለ
የፓራኦሎምፒክ ሻምፒዩኑ ኦስካር ፒስቶሪየስ በቀጣዩ ሳምንት ከእስር ቤት እንደሚለቀቅ የደቡብ አፍሪካ ኮሬክሽናል ሰርቪስ ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡
እጮኛውን ሬቫ ስቲንካምፕን 2013 ተኩሱ በመግደሉ የታሰረው አትሌቱ እንዲለቀቅ የእጮኛው ቤተሰቦች ድጋፍ በማድረጋቸውና የይቅርታ ቦርዱ የታሳሪውን  



Monday, October 19, 2015

የኢትዮ ኖርዌይ ራዲዮ Radio News

ጤና ይስጥልኝ ይህ የኢትዮ ኖርዌይ ራዲዮ ሳምንታዊ የዜና ዘገባ ነው ዜናውን የማሰማችሁ ርሴማ መድህኑ ንኝ በመጀመርያም በይት የዘገባ ዕርዕሶችን
ዩኒቨርስቲው በትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ውይይት በተጠመደበት፤
ከውሃ ብክለት ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪው ሲሞት ሌሎች ሆስፒታል ገብተዋል

ግብጽ በግድቡ ዙሪያ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እፈልጋለሁ አለች





Friday, October 9, 2015

ኢትዮጵያ አምስት ዕንቁዎቿን በድንገት ተነጠቀች


በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመን የውጪ ጉዳይ  ሚኒስትር ከነበሩት አቶ አክሊሉ ሐብተወልድ ጋር በቅርበት የመስራት ዕድል አጋጥሟቸው የነበሩት ጋዜጠኛው  ዘውዴ ረታ ከጋዜጠኝነት ሞያቸው ባሻገር አገራቸውን በአምባሳደርነት ማገልገላቸውን በመጠቀም ያገኟቸውን ሰነዶች፣ልምዶች፣የአይን እማኝነታቸውን ፣የተለዋወጧቸውን ደብዳቤዎች በመጠቀም ሶስት ታላቅ ቦታ የሚሰጣቸውንና ከፍተኛ የምርምር ስራ የተደረገባቸውን  ጠብሰቅ ያሉ የታሪክ  መጻህፍት  አበርክተዋል፡፡

--የኤርትራ ጉዳይ
--ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የስልጣን  ጉዞ
--የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ መንግስት የዘውዴ ዘመን አይሽሬ ስራዎች ናቸው፡፡
በቅርቡ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ታሪክ ላቅ ያለ ቦታ በሚሰጧቸው በአቶ ከተማ ይፍሩ ዙሪያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ መጀመራቸውን ተናግረው ነበር፡፡ዘውዴ አጼ ኃይለ ስላሴን በዋናነት ኤርትራን ከእናት አገሯ ኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን ለማዋሃድ የሄዱበትን ርቀት በማድነቅ አሁንም ሁለቱ አገራት ወደቀደመው አንድነታቸው እንደሚመለሱ ተስፋ ማድረጋቸውንም ተናግረው ነበር፡፡
‹‹በትክክል መቼና እንዴት የሚለውን አላውቅም›› የሚሉት አምባሳደሩ ሁለቱ አገራት አንድ አይነት ታሪክ፣ባህል፣ሃይማኖት፣ስነ ልቦና ያላቸው በመሆኑ በአንድነት ቢቆሙ የበለጠ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡እናም አሁን ያለው ሁኔታ ይህንን ለማድረግ ባይፈቅድም ሁኔታዎች ሲቀየሩ ነገሮች ይለወጣሉ የሚል ተስፋ አለኝ››ብለውም ነበር፡፡ዘውዴ ረታ ብዙ ህልምና ተስፋ እንደሰነቁ ባሳለፍነው ሳምንት በድንገት ለንደን ውስጥ መንገድ ላይ እየሄዱ ወድቀው መሞታቸው ተሰምቷል፡፡የ71 ዓመቱ ዘውዴ እጅግ ተግባቢ፣ሚዛናዊና ቅንነትን የተሞሉ በጎ ኢትዮጵያ እንደነበሩ ወዳጆቻቸው ይመሰክሩላቸዋል፡፡ከዘውዴ ቀደም ብሎ በተመሳሳይ መልኩ በድንገት ለህልፈተ ህይወት መዳረጉ የተሰማው አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ነው፡፡
ጋዜጠኛ  ሙሉጌታ ሉሌ  በማስታወቂያ እና መርሐ ብሔር ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል፡፡ በነፃው ፕሬስ ውስጥ የአክፓክ አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ፀጋዬ ገብረመድህን አርዓያ ና ስንሻው ተገኝ በሚባሉ  የብዕር ስሞች  የማይጠገቡ ፅሁፎችን ጦቢያ በተሰኘ መጽሔት ሲያስነብቡን ቆይተዋል፡፡
 "አጥፍቶ መጥፋት" የሚል በጊዜው ብዙ የተነበበ እና ያወዛገበ መጽሐፍም ፀሐፊ ናቸው፡፡ እኚህ በስራቸው ታላቅ መሆን የቻሉ ሰው በድንገት አረፉ የሚለው ዜና ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡
ህልፈታቸውን  የበለጠ አሳዛኝ  የሚያደርገው  ማስታወቂያ  እና መርሐ ብሔር ሚኒስቴር ውስጥ ሲሰሩ የስራ ባልደረባቸው (አለቃቸው) የነበረው ጋዜጠኛ እና ደራሲ በዓሉ ግርማ እንዴት እንዳለፈ የሚያውቁትን ያህል ሳይነግሩን ወይም ሳይፅፉልን ማለፋቸውን ስናስብ ነው፡፡ ስለ በዓሉ ህልፈት ምስጢር ፍቺ የተፃፉ ጽሁፎች ሁሉ የጋሽ ሙሉጌታን ስም ያነሱ ነበር፡፡ ብዙ ምስጢር እንደሚያውቁም ይጠቁሙ ነበር፡፡ በእርሳቸው፣ ገዳሙ አብረሃ እና በዓሉ መካከል ስላለው ፉክክር እና ቅራኔ ዝርዝር ይተረኩ ነበር፡፡
የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በአሜሪካ ተፈጽሟል፡፡ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ፣ዶክተር ሽመልስ ተ/ጻድቅና የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት የጀርባ አጥንት የነበሩት ባለሃብቱ አቶ አቤሴሎም ይህደጎም ያረፉት ከሰሞኑ ነበር፡፡ ኢቴኒኮ በአምስቱ  የኢትዮጵያ እንቁ ልጆች ህልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ለሞያ ባልደረቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል፡፡ 

Monday, October 5, 2015

አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ማጣት ለኢትዮጵያ ትልቅ ጉዳት ነው …


አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ማጣት ለኢትዮጵያ ትልቅ ጉዳት ነው …ጋሽ ሙሉጌታ ትሁት፣አዳማጭ፣የማስታወስ ችሎታው የሚያስገርም ነው። ተንቀሳቃሽ ቤተ መጽሐፍት ማለት ይቻላል > የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ የቀድሞ የጦቢያ መጽሔትና ጋዜጣ አዘጋጅ አንተነህ መርድ ከህብር አዘጋጆች ጋር ባካሄደው ውይይት ከተናገረው 
<…ዕውቁ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ መምህርም ነበር ካስተማራቸው መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገኙበታል ፣ለኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ፈር ቀዳጅ ፣ ዲፕሎማት ጭምር ነበር። ለ18 ጊዜያት በዚህ ስርዓት ተከሷል ተገፍቶ ተሰዷል እስከ መጨረሻ ግን ለሙያው እና ለዕውነት ታማኝ እንደሆነ ያለፈ ታላቅ ሰው ነው..> 

Thursday, October 1, 2015

የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ካለው 30ኛ ጉባኤ ስብሰባ ረግጠው ወጡ

All members with the exception of Russia's UN Ambassador Vitaly Churkin and China's deputy U.N. Ambassador Wang Min vote in the United Nations Security Council in favor of referring the Syrian crisis to the International Criminal Court for investigation of possible war crimes at the U.N. headquarters in New York May 22, 2014. REUTERS/Lucas Jackson (UNITED STATES - Tags: POLITICS) - RTR3QEAZ
ተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ካለው 30ኛ ጉባኤ ጋር ተያይዞ በተጠራ መድረክ ላይ የተጋበዙት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ስብሰባ ረግጠው ወጡ። ስኞ እለት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት በተመለከተ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙትና በኋላ በቀረበው ሪፖርት ሳይደሰቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ወደ ስብሰባው አልተመለሱም። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች በጄኔቭ ስዊዘርላንድ በመገኘት በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት አያያዞች ዙሪያ መወያየታቸውን እማኞች አስታውቀዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በመድረኩ ሊነሱ በሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ከጉባኤው ረግጠው መውጣታቸው