Thursday, June 18, 2015

የእንግሊዝ መንግስት በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ስጋት እንደገባው ለቤተሰቦቹ አስታወቀ


በቀጣዩ ሳምንት የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ታፍነው ወደ አዲስ አበባ ከተወሰዱ ድፍን አንደ ዓመት ይሆናቸዋል፡፡


አንዳርጋቸው እጃቸው ከመያዙ አስቀድሞ በሌሉበት የኢትዮጵየ ፍርድ ቤቶች የሞት ፍርድ ያስተለለፉባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንደተነገረም መንግስት ቀደም ብሎ ያስተላለፈባቸውን የሞት ውሳኔ ተፈጻሚ ሊያደርግባቸው እንደሚችል በመስጋት ብዙዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡

በአዲሰ አበባ የሚገኙት የእንግሊዝ አምበሳደር አንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸው ቢነገርም
ፈቃድ ያገኙባቸው አገጋጣሚዎች በጣም አነስተኛ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ሪፖርቱ አምበሳደሩ አንዳርጋቸውን ከጎበኙ በኋላ ምንም የተሻሻለ ነገር አለመኖሩን መጥቀሱ የአንዳርጋቸውን ባለቤት ክፉኛ እንዳሳዘናቸው ለጋዜጣው እንደነገሩት አስፍሯል፡፡ሪፖርቱን ለወይዘሮ የሚ የሰጧቸው በእንግሊዝ የውጪ ገዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኛ ሳራ ዊንተር ‹‹የሪፖርቱ የተወሰኑ ነጥቦች የሚየሰጨነቀቁ በመሆናቸው በምታነቢያቸው ወቅት በአጠገብሽ ሰዎች እንዲገኙ አድርጊ ››በማለት ሊመክሯቸው እንደሞከሩ ወይዘሮዋ ተናረዋል፡፡
እንግሊዛዊው አምባሰደር ግሬግ ዶሬ በኤፕሪል የሶሰት ልጆች አባት የሆነትን አንዳርጋቸውን ለደቂቃዎች እንዲጎበኙ ከተደረጉ በኋላ ስለጉብኝታቸው የሚየስረዳ ሪፖረት ለአንዳርጋቸው ባለቤት ያሚ አንዳርጋቸው መላኩን ዘ ኢንዲፐንደንት የተሰኘው ጋዜጣ ለንባብ አብቅቷል፡፡
የአምባሳደሩ ጉብኝት አንዳርጋቸው በሚገኙበት ይፋ ያልሆነ ወህኒ ቤት የተከናወነ ካለመሆኑም በላይ በዙሪያቸው ፖሊሶች የነበሩ በመሆናቸው እንደልብ መነጋገር አለመቻላቸውም ተወስቷል፡፡
አምበሳደሩ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው በመጥቀስ ለወይዘሮ ያሚ‹‹ሰብአዊነት ጭምር በመሆኑ ለመሄድ ደስተኛ ነኝ፡፡መንግስት አንዳርጋቸውን በሞት ለመቅጣት በመፈለጉ ዙሪያ ጥርጣሬ ያለኝ ቢሆንም ይህ እንዳይፈጸም ጠንክረን በመርህ ደረጃ አነንራለን››ማለታቸውን ሪፖርቱ አስታውሷል፡፡
የአንዳርጋቸው አካላዊ ደህንነት ደህና ቢመስልም የጤንነት ሁኔታቸውን በተመለከተ ግን ሀሳብ ገብቷቸዋል፡፡የቀረቡበት ሁኔታም ከስነ ልቦና ረገድ በጣም መጥፎ ሊሰኝ የሚገባው ነው፡፡በታሰሩበት ቦታ ምን አይነት ነገሮች እየደረሱበቸው እንደሚገኙ የሚያሳዩ መረጃዎችን ማግኘት አልተቻለም ብሏል ሪፖርቱ፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ አንዳርጋቸው በህይወት ለመቆየት ተስፋ የሚያደርጉበትን ምክንያት ማየት አልቻሉም:: በእርሳቸው ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት እየተደረገ እንደነበር ማወቃቸው መጠነኛ እፎይታ ሳይፈጥርላቸው አልቀረም ብሏል፡፡ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ጠባቂዎቻቸው ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ በማለት ይሰጉ እንደነበር በመጥቀስ እርሳቸው ግን ሞክረውት እንደማያውቁ ለአምባሳደሩ ነግረዋቸዋል ፡፡
ወይዘሮ ያሚ ‹‹ደበዳቤው ከተጻፈ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፤ነገር ግን የተለወጠ ነገር የለም፡፡ተስፋ መቁረጥ ውስጥ አገኛለሁ፡፡በኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ አይነት ነገሮች እያጋጠማቸው አምባሰደሩን ካላስቆጣቸውነ ጉዳዩን የምር መውሰድ ካልቻሉ ምንድን ነው ጥቅሙ ? ›› በማለት በምሬት መጠየቃቸውን ዘ ኢንዲፐንደንት አስነብበቧል፡፡
በሰሜን ለንደን የሚኖሩት የአንዳርጋቸው ባለቤት ሪፖርቱን ከተመለከቱ በኋላ ‹‹ሪፖርቱ ስለያዛቸው ነገሮች ተነግሮኝ የነበረ ቢሆንም ወረቀቱን በጥቁርና ነጭ ስመለከተው በጣም ነው የተበሳጨሁት ማለታቸውን ጋዜጣው አስነብቧል፡፡
የእንግሊዙ የውጨ ጉዳይ ሚንስትር ፊሊፕ ሃሞንድ ለኢትዮጵያ አቻቸው ደብዳቤ በመጻፍ በአንዳርጋቸው ላይ አንዳች ክፉ ነገር ቢደርስ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ ግኑኝነት ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር በማስጠንቀቅ አንዳርቸው ህክምና እንዲያገኙና በመደበኛ እስር ቤት ታስረው በጠያቂዎች እንዲጎበኙ እንዲያደርጉ የጠየቁ ቢሆንም ምንም ለውጥ አለመተየቱ የአንዳርጋቸውን ባለቤት አሳስቧል፡፡

No comments:

Post a Comment