Wednesday, June 3, 2015

በቃ ጓደኞቻችንን ፍቱልን!!!



መቼምሐብታሙአያሌው፣ዳንኤልሺበሺ፣አብርሃደስታ፣የሺዋስአሰፋ፣ብርሃኑ ተክለያሬድ፣እየሩሳሌም፣ዘላለም፣በፍቄ፣ናቲ፣አስሚቲ፣አቤሎ፣ማሂ፣ተስፋለም፣ተመስገን፣አለማየሁ፣መሳይ፣ስንታየሁ እና ብዙዎቹን የቀማችሁን ያስጠናችኋቸው ‹‹የአቃቤ ህግ ››ምስክሮች ጭምር ሊሸመድዱት ባልቻሉት ‹‹ልብ ወለዳዊ››ወንጀል መሆኑን እናንተም፣ታሳሪዎቹም፣መስካሪዎቹም፣አቃቤ ህጉም ፣ዳኛውም ሆነ እኛም እናውቀዋለን፡፡
ይህንን ሁሉ ወጣት ጠራርጋችሁ የወህኒያችሁን ስፋት የለካችሁባቸው የማሰር ሱስ ይዟችሁም እንዳልሆነ ሁላችንም
እናውቃለን፡፡እስክንድር ነጋ ‹‹በፍርድ ቤት ያቀረቡብኝ ክስ እኔን እንደማይወክል እነርሱም ያውቁታል፡፡በትክክል ግን የስልጣናቸው ስጋት መሆኔን ስለሚያውቁ ሰበብ ፈጥረው አስረውኛል››የሚለውም የልባችሁ ፍርሃት ገብቶት ነው፡፡ ዕድሜ ልክ የፈረዳችሁበት አንዷለም አራጌም አልተቀየማችሁም፡፡ይህንን ማረጋገጥ ካሻችሁ ቀዝቃዛው ስሚንቶ እየሞቀው የጻፈውን ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› መጽሃፉን አንብቡለት፡፡ አሁን ስጋታችሁ አልፎ ምርጫውን ካለፈው በተሻለ ሪከርድ መስበራችሁን ለማብሰር የቀራችሁ ‹‹የምርጫ ቦርድ››ደወል ብቻ ነው፡፡ታዲያ የምርጫችሁ ስጋት የነበሩ ልጆች ከአሁን በኋላ በወህኒ ቤታችሁ ምን ያደርጋሉ? በቃ ፍቷቸው፡፡ባይሆን የሚቀጥለው ምርጫ ከመድረሱ በፊት መልሳችሁ ልታስሯቸው ትችላላችሁ፡፡

No comments:

Post a Comment