Here is the ETNK-TV Weekly News!!
Sunday, June 28, 2015
Wednesday, June 24, 2015
Obama's plan to visit Ethiopia criticised as 'gift' for repressive government
Barack Obama’s decision to visit Ethiopia has shocked human rights activists, who say the visit sends the wrong message to a repressive government widely accused of clamping down on dissent.
A White House statement said Obama will visit the east African country for meetings with government officials as part of
JOURNALISM IS NOT A CRIME!!!!
JOURNALISM IS NOT A CRIME!!!!
Watch the two minutes video produced as a tribute to Tesfalem Waldeyes. This was first showed during a presentation “Too Scared
Monday, June 22, 2015
Sunday, June 21, 2015
ሰማያዊ ፓርቲ “ከፍተኛ አመራሮችና አባላቶቼ በሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ” ሲል አስታወቀ
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዛሬ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አቀወ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች
Thursday, June 18, 2015
ሰማያዊ ፓርቲ አባሉን ገድለዋል ከተባሉ ተጠርጣሪዎች አንዱ በቁጥጥር ስር ዋለ
በደብረማርቆስ ከተማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የነበረው አቶ ሳሙኤል አወቀ በደረሰበት ድብደባ ከትናንት በስቲያ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም ምሽት ህይወቱ ማለፉ ታወቀ። አቶ ሳሙኤል አወቀ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆኑና በፖለቲካዊ አቋሙ ምክንያት የተለያዩ ዛቻዎችና ማስፈራሪያዎች በተደጋጋሚ ይደርሱት እንደነበር የሚናገሩት የፓርቲው የህግ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ፤ ከዚህ ቀደምም በተፈፀመበት ድብደባ የአካል ጉዳት ከማጋጠሙም ባለፈ ታስሮ እንደነበር ተናግረዋል።
ሰንደቅ ጋዜጣ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን
የእንግሊዝ መንግስት በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ስጋት እንደገባው ለቤተሰቦቹ አስታወቀ
በቀጣዩ ሳምንት የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ታፍነው ወደ አዲስ አበባ ከተወሰዱ ድፍን አንደ ዓመት ይሆናቸዋል፡፡
አንዳርጋቸው እጃቸው ከመያዙ አስቀድሞ በሌሉበት የኢትዮጵየ ፍርድ ቤቶች የሞት ፍርድ ያስተለለፉባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንደተነገረም መንግስት ቀደም ብሎ ያስተላለፈባቸውን የሞት ውሳኔ ተፈጻሚ ሊያደርግባቸው እንደሚችል በመስጋት ብዙዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡
በአዲሰ አበባ የሚገኙት የእንግሊዝ አምበሳደር አንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸው ቢነገርም
Friday, June 5, 2015
ዲና መፍቲን ያንብቧቸው ‹‹መለስ ቤትና መኪና የሌለው ብቸኛው አፍሪካዊ መሪ ነው››
በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተደርገው በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዘዳንት ያስገቡት ዲና መፍቲ ከኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ጋር በተለያዩ ጉዳዩች ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡አስገራሚ ምለሾችን አምባሳደሩ የሰጡበትን ቃለ ምልልስ ወደ አማርኛ መልሼዋለሁ ይመለከቱት ዘንድ ግብዣዬ ነው፡፡ዲና በኢንተርቪያቸው
--መለስ ዜናዊ የግል መኪናም ሆነ ቤት እንዳልነበራቸው ተናግረዋል
-በኬንያ በስደት የሚገኙት ጋዜጠኞች ‹‹ጋዜጠኞች ›› አለመሆናቸውን ገልጸዋል
--ኢትዮጵያ ነጻ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በየአምስት አመቱ የምታከናውን ዴሞክራሲያዊት አገር ናት ብለዋል
ጥያቄ -- ወደ ዱባይ ያቀና ነበረው የኡሁሩ ኬንያታ ጄት ወደ መነሻው እንዲመለስ የመደረጉ ምክንያት ኢትዮጵያ መሆኗ ከታወቀ በኋላ ለጥያቄ በኬንያ ሃላፊዎች ተጠርተው ነበር--
ዲና --ከየትኛውም ወገን ጥሪ አልቀረበልኝም፡፡ከምገኝባት አገር ሰዎች ጋር ተገናኝቼያለሁ ይህ ደግሞ በዴፕሎማሲው መስክ የተለመደ ነገር ነው፣ ስለዚህ ጥሪ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡
ጥያቄ --ኢትዮጵያ ግን የፕሬዘዳንቱን ጄት አስቁማለች?
ዲና --በዚህ ዙሪያ አስተያየት አልሰጥም፡፡
ጥያቄ --ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ረዘም ያለ ድንበር ብትጋራም አልሻባብን ማስፈራት የቻለች ትመስላለች፡፡ኬንያ ማድረግ የተሳናት ኢትዮጵያ ግን ማድረግ የቻለችው ነገር ምንድን ነው?
ዲና --የትኛውም አገር በአፍሪካም ይሁን በምዕራቡ አለም የሚገኝ ሽብርተኝነትን አጥፍቺያለሁ ማለት አይችልም፡፡በአንጻራዊነት ኢትዮጵያ ግን ስኬታማ ሆናለች፡፡ምክንያቱም በደህንነቱና በህዝቡ መካከል ጥሩ የሆነ ትብብር በመኖሩ ነው፡፡ህዝቡ ጠቃሚ የሆነን ኢንፎርሜሽን በመስጠቱ የሽብርተኝነት ህዋሶች እንዲጋለጡና እንዲጠፉ አድርጓል፡፡
ኬንያም እየተገበረች የምትገኘው ፍልስፍናም ተመሳሳይ ነው፡፡በኒዩምባ ኩሚ እያንዳንዱ ዜጋ የደህንነት ሰራተኛ ነው፡፡መንግስትም በማዳራሳ ጥሩ የሚባል ግኑኝነት ከሐይማኖት መምህራን ጋር አለው ይህም የእስልምና አስተምህሮ አክራሪነትን እንደማያበረታታ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የጸጥታ ሰራተኞች የአገራቸውን ደህንነት ከምንም ነገር በላይ እንዲያስቀድሙ በአርበኝነት አስተምህሮ እንዲጠመቁ በመደረጋቸው በሽብርተኝነት አስተምህሮ ሊበላሽ አይችልም፡፡
ጥያቄ -በቅርቡ በኬንያና ኢትዮጵያ የጋራ ወሰን አካባቢ ዘራፊዎች በኢትዮጵያ ወራሪዎች ኬንያን አጥቅተዋል፡፡ለእንዲህ አይነት ድርጊት ኬንያ ኢትዮጵያዊያኑን በማጥቃት የአጸፋ ምላሽ መስጠት አለባት?
ዲና -- የወሰን አካባቢ ግጭቶች ሁለቱ አገራት የሚገኙበትን አስደሳች ሁኔታ አያንጸባርቁም፡፡ይህ በኬንያ በሚገኙ ጎሳዎችና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ጎሳዎች ሊያጋጥም ይችላል፡፡ለማንኛውም የድንበር አካባቢ ግጭቶችን ሁለቱ መንግስታት በአካባቢው የሚገኙ ማህበረሰቦችን ትርጉም ባላቸው የልማት እንቅስቃሴዎች በማሳተፍ ሊያስወግዱ አልያም ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡
ጥያቄ --በቅርቡ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሐይሎች 16 ኪሎ ሜትር ወደ ኬንያ በመግባት በዚያ የሚገኘውን የፖሊስ ጣብያ ተቆጣጥረው ነበር ….
ዲና -ይህንን ክስ የኬንያ ፖሊስ ቃል አቀባይ በግልጽ አስተባብለዋል፡፡ኢትዮጵያ ከአል ሻባብ ጋር በምታደርገው ጦርነት ኬንያ የኢትዮጵያ ጠንካራ ተባባሪ ናት፡፡በታሪክ ውስጥ ሁልግዜም ለኬንያዊያን ቅርብ ነን፡፡የውስጥ ችግር በነበረን ወቅት ኬንያ ለኢትዮጵያ ስደተኞች የሰላም ደሴት በመሆን አገልግላለች፡፡ስለዚህ በኢትዮጵያ ወታደሮች በኬንያ ላይ የተደረገ ወረራ ከዚህ በፊት እንዳልነበረ ሁሉ ወደፊትም አይኖርም፡፡
ጥያቄ--የኬንያ የንግድ ሰዎች በኡጋንዳ ፣ሩዋንዳና ደቡብ ሱዳን በከፍተኛ መጠን ይገኛሉ፡፤ለምንድን ነው ወደ ኢትዮጵያ የማይሄዱት ? ኢኮኖሚያችሁ ክፍት ወይስ ቁጥጥር የሚደረግበት ነው ?
ዲና --የእኛ ኢኮኖሚ ለሁሉም ኢንቨስተር ክፍት ነው፡፡ ብዙ የኬንያ የንግድ ሰዎች በኢትዮጵያ በመገኘት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በኬሚካል ኢንዳስትሪ መዋዕለ ነዋያቸውን አፍስሰዋል፡፡በእርግጥ ኬንያዊያኑ ይህንን በማድረግ ከግብጽና ሱዳን በመለጠቅ ሶስተኛ ናቸው፡፡
ጥያቄ --ብዙ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ በህገ ወጥ መንገድ በመግባታቸው ታስረዋል፣ሌሎች በሊቢያ ለመሞት አሁንም እየሄዱ ነው የተወሰኑት ደግሞ በአይ ኤስ አይ ኤስ ተገድለዋል…
ዲና --እነዚህ የታሰሩት በሰው አዘዋዋሪዎች በውጪ አገር ገነትን የመሰለ ህይወት ትኖራላችሁ ተብለው ተስፋ የተገባላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ በአብዛኛው ወጣትና ከገጠራማ የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ ናቸው፡፡የሚበዙት ኢትዮጵያዊያን ግን በአገር ውስጥ እየተፈጠረ በሚገኘው ዕድል በመጠቀም ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊት አገር በመሆኗ ነጻና ተአማኒነት ያለው ምርጫ በየአምስት አመቱ የምታደርግ በመሆኗ ወታደራዊ አገዛዝ የሰፈነባት ናት ማለት አይቻልም፡፡
ጥያቄ -ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች በኬንያ በስደት ላይ ይገኛሉ፣ በዚህ ላይ ስድስት የሚታወቁ ጦማሪዎችና ሶስት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ናቸው አይደለም እንዴ አምባሳደር ?
ዲና --የኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነት ምህዳር በጣም ለጋ ነው፡፡የተጀመረውም በ1991 ኢህአዴግ ወደ ስልጣን እንደመጣ ነው፡፡ስለዚህ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ነገር ግን የማንፈቅደው ነገር ምንድን ነው ሰዎች በጋዜጠኝነት ካባ ተሸፍነው ዜጎችና ጎሳዎችን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ እንዳያነሳሱ ነው፡፡ስለዚህ በኬንያ የሚኖሩት እውነተኛ ጋዜጠኞች አይደሉም፡፡የስድስቱ ጦማሪያንና የሶስቱ ጋዜጠኞች ጉዳይ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የሚገኝ በመሆኑ አስተያየት መስጠት አልችልም፡፡
ጥያቄ -- መለስ ዜናዊ ከሞቱ ሶስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡እንዳጣችሁት ይሰማችኋል ?
ዲና --እንደ ህዝብ በጣም አጥተነዋል፡፡ምክንያቱም እርሱ የኢትዮጵያ የህዳሴ አባት ነበር፡፡የግሉ መኪና እና መኖሪያ ቤት ሳይኖረው የሞተ ብቸኛ አፍሪካዊ መሪ እርሱ ነው፡፡ መለስ አገልጋይ መሪ ነበር፡፡የቀድሞው መለስ የራሱን ስብእና ከመገንባት ይልቅ የስርዓት ሰው ነበር፡፡ጠንካራ ስርዓትን ዘርግቶ በማለፉም ከእርሱ ስንብት በኋላም በእርሱ ስርዓት እየሄድን እንገኛለን፡፡
ጥያቄ --ኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ባቡር ግንባታን በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ይህ በኬንያ ከሚገኘው በመጠኑ የሚተልቅ ቢሆንም ወጪው አነስተኛ ነው፡፡ይህ እንዴት የሚቻል ሆነ ?
ዲና --በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅና ዝርዝር መረጃ የለኝም፡፡ምክያቱም የሰለጠንኩበት ዘርፍም አይደለም፡፡ነገር ግን እንደ አገር ሙስናን መቀነስ በመቻላችን በአስገራሚ ሁኔታ ከአንዳንድ ፕሮጀክቶች ወጪ መቀነስ ችለናል፡፡
ጥያቄ --አዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የሚያስችሏትን (እንደ ባቡር ያሉ) መኪኖች አገልግሎት መስጠት ጀምራለች፡፡ይህ በአውሮፓ አገሮች በጣም የተለመደ ነው፡፡ናይሮቢ ከዚህ መውሰድ የምትችለው ነገር ምንድን ነው
ዲና --አዎን ላለፉት ሶስት ወራቶች በሌሎች ከተሞች ጭምር የሙከራ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡
ናይሮቢም አቅሙ ያላት በመሆኑ የትራፊክ መጨናነቁን ለመቀነስ ሐሳቡን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባታል ፡፡ በአዲስ አበባ ሙከራው የትራፊኩን መጨናነቅ ሲቀንስ ተመልክቻለሁ፡፡
Thursday, June 4, 2015
ኢትዮጵያዊያኑ የኬንያን ፍርድ ቤቶች እያጣበቡ ነው
ከኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ በረራ ቪዛ ማግኘት ካለፉት አስር ዓመታት ጀምሮ ለኢትዮጵያዊያን ፈጽ ሞ የማይታሰብ ሆኗል፡፡በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ደረጃ ቁጥራቸው እየተበራከተ በመምጣቱ አዲስ አበባ የሚገኘው የኔልሰን ማንዴላ አገር ኢምባሲ ቪዛ መስጠት ዳገት ሆኖበታል፡፡
ህጋዊው መንገድ እየጠበበ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ የሚያስፈልገውን ፈቃድ ማግኘትም 100.000 ብሮችን መስዋዕት ማድረግን ሲጠይቅ የተሻለ ህይወት በደቡብ አፍሪካ እንደሚገኝ የሚሰሙት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ወደ ኬንያ በማቅናት
Wednesday, June 3, 2015
በቃ ጓደኞቻችንን ፍቱልን!!!
መቼምሐብታሙአያሌው፣ዳንኤልሺበሺ፣አብርሃደስታ፣የሺዋስአሰፋ፣ብርሃኑ ተክለያሬድ፣እየሩሳሌም፣ዘላለም፣በፍቄ፣ናቲ፣አስሚቲ፣አቤሎ፣ማሂ፣ተስፋለም፣ተመስገን፣አለማየሁ፣መሳይ፣ስንታየሁ እና ብዙዎቹን የቀማችሁን ያስጠናችኋቸው ‹‹የአቃቤ ህግ ››ምስክሮች ጭምር ሊሸመድዱት ባልቻሉት ‹‹ልብ ወለዳዊ››ወንጀል መሆኑን እናንተም፣ታሳሪዎቹም፣መስካሪዎቹም፣አቃቤ ህጉም ፣ዳኛውም ሆነ እኛም እናውቀዋለን፡፡
ይህንን ሁሉ ወጣት ጠራርጋችሁ የወህኒያችሁን ስፋት የለካችሁባቸው የማሰር ሱስ ይዟችሁም እንዳልሆነ ሁላችንም
Tuesday, June 2, 2015
ከዚህ በላይ ሰላማዊነት ይኖር ይሆን?
እንደ አንድ አባት አሳድገው ትውልድን መቅረጽ ወደሚያስችላት የመምህርነት ሞያ ያደረሷትና ታናሽ እህቷ (እስከዳር አለሙ)ከዚህ ቀደም እንደተረከችልን ከልጅነቷ ጀምሮ አብሯት የዘለቀውን የጋዜጠኝነት ተሰጥኦዋን አውጥታ ለግፉአን ድምጽ እንድትሆን ያበረቷት ልጃቸው ጠመኔ ጨብጣ ከምታስተምርበት አስኳላ በመንግስት ሐይሎች ታፍና ተወስዳ በመንግስት አፍ ‹‹የአገሪቱን መሰረተ ልማቶች የማፈራረስ ትዕዛዝ ተቀብላ በቁጥጥር ስር ስለ መዋሏ ሲነገር አቶ ዓለሙ ጎቤቦ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል ‹‹አባትነት›› ለሆነላቸው ሁሉ የሚሰወር አይመስለኝም፡፡
አቶ ዓለሙ ለጋዜጠኛና መምህርት ልጃቸው አባት ከመሆናቸው ባሻገር በሞያቸው ጠበቃ ናቸው፡፡የአገሪቱ ህገ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በተመለከተ ምን እንደሚል ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ሳያገኙ ቃል ያለመስጠት መብት እንዳላቸው ይህንኑ መብት የማክበር ግዴታ ፖሊስ እንዳለበት ጠበቃው ይረዳሉ፡፡
ልጃቸው የምትገኝበትን ሁኔታ እንደ አባት የማወቅ መብት ቢኖራቸውም በሞያቸው ጥብቅና ሊቆሙላት የሚችሉ መሆናቸውም የአቶ ዓለሙን መብት ድርብርብ ያደርገዋል፡፡ርዕዩት ወደምትገኝበት ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ልጃቸውን በማየት ተስፋ ተሞልተው አመሩ‹‹አባትም ሆኖ ጠበቃ በዚህ ወቅት ርዕዮትን ማየት አትችሉም አሏቸው››፡፡
ለርዕዮት አባትም ጠበቃም ለሆኑት አቶ ዓለሙ ይህ ሊቀበሉት የሚችሉት አልነበረም ግን ህገ መንግስቱን ሌሎችን ለማጥቂያነት የሚጠቀሙበት ጉልበተኞች ምድሪቱን በመቆጣጠራቸው አቶ ዓለሙ ልጃቸውን
Subscribe to:
Posts (Atom)