ሽልማቱን የሰጠው የ ኤርትራ ፕረስ ነው። ለ600 000 ሳምንታዊ አንባቢዎቹ መልካም ለ2016 ምኞቱን በመግለጽ ነው ዜናውን ያበሰረው ፕረሱ። የተንደላቀቀ ኖሩውን በመተው የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ አምባ ገነን አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የነፃነት ታጋዮችን በመቀላቀሉ ለሽልማቱ ተመርጧል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ለማምጣት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም ይላል ፕረሱ። በመጫረሻም የመጨረሻውን አማራጭ የትጥቅ ትግል መጀመር ብቸኛው ምርጫ ሆኖ አገኘው። ራስ ወዳድነትን ያሰወገደና ድፍረትን የተላበሰ ውሳኔው የ2015 የ ኤርትራ ፕረስ ምርጥ ሰው እንዲሆን ዋና ምክንያት ሆኗል። በ 1958 በደብረ ዘይት ከተማ የተወለደው ፕሮፌሰር ብርሐኑ ከወጣትነቱ ጀምሮ የነፃነት ታጋይ እንደነበረ ተገልጿል። ሱዳን ሁለት አመት እንደኖረና በአማሪካን አገር ጥገኝነት ዋስትን በማግኘቱ ወደ አሜሪካ መጓዙን ፕሪሱ ገልጿል። የመጀሪያና ድግሪውንና የፍልስፍና ድግሪውን በምጣኔ ሀብት ላይ መስራቱን ይዘግባል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ በቡከኔል ዩኒቨርስቲ ለ3 አመት በመምህርነት አገልግሏል። በ 1989 የተቓቓመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሞያዎች ማህበር መስራች አባል መሆኑንም ፕሬሱ ያትታል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ አሜሪካን አገር የተወለደችውንና ይቻላል የሚል አስተሳሰብ ያላትን ዶር ናርዶስን አገባ። በ 2005 ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ ቅንጅት አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ በማሸነፉ ዶር ብርሐኑ ከንቲባ ሆኖ ተመረጠ። ፕሮፌሰር ብርሀኑ የ አርበኞች ግንቦት ሰባት መሰራች አባል መሆኑ ይታወቃል ሲል የ ኤርትራ ፕረስ አስታወቀ። የ ኤርትራ ፕሪስ ሽልማቱን ይፋ ያደረገው ዴሴምበር 31 2015 ነው።
No comments:
Post a Comment