Tuesday, January 12, 2016

“ለድለላ” ሕወሃት ከፍተኛ የጦር አዛዥነት ሹመት ሊስጥ ነው! “እንዴት ጠባቦች ይጫወቱብናል?”



tplf generalsሕወሃት የከፍተኛ መኮንኖች “የመደለያ” ሹመት ለመስጠት ማቀዱ ተሰማ። አባይ ጸሃዬ ለህዝባዊ ተቃውሞው የተሰጠው መልስ የተለሳለሰ ነው አሉ። ህዝባዊ አመጹ ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን ኢህአዴግ ይፋ አደረገ። ግርፋት፣ ግድያ፣ እስር፣ እንግልትና ስደት ያሳሰባቸው ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ የመከላከያ መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ እንዳመለከተው፣ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ አለመግባባቱና መቃቃሩ ከሯል። በሠራዊቱ ውስጥ የአንድ ብሔረሰብ አባላት ፈላጭ ቆራጭነት የፈጠረው ልዩነት መባባሱ አሁን ከተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ ጋር ህወሃትን አሳስቦታል። አርዶታል።
እንደ ዘጋቢያችን ገለጻ ኢትዮጵያን በተገንጣይ ስም እየመራ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሃት) አሁን በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኛነት ወደ ሌላ ክልል እንዳይዛመት ሰግቷል። ለዚህም አንዱ የስጋት ማስተንፈሻ ተደርጎ የተወሰደው በመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ዘንድ ያለውን ውጥረት “በመደለያ” ሹመት ማስተንፈስ ነው።
“የታቀደው ሹመት መደለያ ነው። የመጀመሪያ ተሹዋሚ ይሆናሉ ተብሎ የተያዙት ባብዛኛው የኦሮሞና የአማራ ልጆች ናቸው” በማለት መረጃውን ያቀበሉት ክፍሎች ሹመቱ እስከ ጄኔራልነት የሚደርስ እንደሆነ አመላክተዋል። የዜናው ምንጮች ሹመቱ ይፋ የሚሆንበትን ጊዜ መቼ እንደሚሆን ግን ሳይገለጹ ቀርተዋል። ሃሳቡ ከመቅረቡ ውጪ ውሳኔ ተሰጥቶበት ተግባር ላይ የሚውለው ቀን ያልገለጹት ምንጮች “አዲስ የሚሰጠው ሹመት ከሙሉ የኃላፊነት ነጻነት ጋር አይደለም” በማለት አስታውቀዋል።
“… የመከላከያ ሠራዊት አባላት የተገነባው በደሃ ልጆች ነው። እባካችሁን እንደናንተው የድሃ ልጆች ወገኖቻቹህን አትግደሉ። ተንደላቃችሁ የምትኖሩም ለዚህ ህዝብ ራሩለት። ለራሳችሁ ጥቅም ስትሉ ይህን ህዝብ አታስፈጁት … የድሃ ልጅ በድሃ ላይ እንዲዘምት መደረጉ ያሳዝናል” ሲሉ አቶ በቀለ ገርባ ለኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት ጥሪ ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ለህወሃት ታማኝ አገልጋይ ሹመኞችም “አሁን በተያዘው መንገድ ከተቀጠለ ለማንም አይበጅም” ሲሉ በግልም ሆነ በጋራ ህዝብን የሚያከብር ታሪካዊ ውሳኔ እንዲወስኑ ተማጽነው እንደነበር የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ ከ140 ሰዎች በላይ የተገደሉበት ህዝባዊ ተቃውሞ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑንን ኢህአዴግ አስታውቋል። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ለመገናኛ ብዙሃን ሲያስረዱ “ችግሩ ከቁጥጥራችን ውጪ ሆኗል። … አሁን በሟቾች ቁጥር የምንከራከርበት ወቅት አይደለም” ብለዋል። የኢህአዴግ አፈቀላጤ ጌታቸው መናገር በተሳነው አንደበት ይህንን ካሉ በኋላ አባይ ጸሃዬ ሰላማዊ ተቃውሞ ባሰሙ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የተወሰደው ርምጃ የተለሳለስ መሆኑንን ያስታወቁበት ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ይፋ ባደረገው የአባይ ጸሃዬ ድምጽ “እየተወሰደ ያለው ርምጃ በቂ አይደለም። በክልልና በፌዴራል መንግሥት መልፈስፈስ ታይቷል” ሲሉ ተደምጠዋል። “እናንተ ደካሞች ናችሁ፣ ጠባቦች እንዴት ይጫወቱብናል?” በማለት ርምጃው የተለሳለሰ በመሆኑ ተጥናከሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። ታህሳስ 20 ቀን 2015 ጎንደር ባንድ ሆቴል ውስጥ በተደረገው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ አባይ ጸሃዬ ሲዛለፉ ተሰምተዋል። ቀደም ሲል “ልክ እናስገባለን” ማለታቸውና ከመሬት ንግድ ጋር በተያያዝ “የመሬት ከበርቴው ሚኒስትር” እንደሚባሉ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። (“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!! በሚል ርዕስ ከዚህ በፊት ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች ይገኛል)

“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!! ምስጢሩን ያጋለጠው መሃንዲስ የት ደረሰ?


abay corruption

አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ።
በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው  ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል።
ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና  ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው።
የኮሚሽኑ የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል።
በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች  ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል።
ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል።
አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜ “ለምን” የሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤  መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ። “ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከር” የሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!!
“ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽን” በሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ።
ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር።
ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበት “እንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነው” በማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ።
መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል።
የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ።
ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱ “በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
“ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውም “በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
“ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስ” የስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ “አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪ “ስርዓቱ በስብሷል” ባይ ናቸው።
“ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነው” በማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውም “ስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነው” በማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ።
የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡
የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በግለሰብ ስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Sunday, January 10, 2016

ኢትዮ ኖርዌይ ራዲዮ 10-01-2016 ዜና




የልደት መዝሙር
ስለ ጋናዊው ፕሮፌሰር ጆርጅ ኣያቴ የዲሞክራሲያው ለውጥ ዘዴ
ቱኒዚያዊዋ ፕሮፌሰር ራግኒድ ጆህንሩድ ዞጋቲ ስለ ቱኒዚያ የዲሞክራሲ ሂዲት

Sunday, January 3, 2016

ETNK weekly report 03-01-2016


የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ?

ከበውቀቱ ስይዮም |03 January 2016


አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ 
(እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ)
የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol
የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ“ እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት“ እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴ በተለያየ ጊዜ ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ እንደ ዘንድሮ ተስፋን፤ ከሻኛውና ከፍሪምባው አፈራርቄ የቆረጥሁበት ጊዜ አልገጠመኝም፡፡

መንግሥትም ሃያ አመት ሙሉ አጥሮ፤ ሃያ ዓመት ሙሉ ቆፍሮ የተሳካለት ኣይመስልም ፡፡ “በየቦታው እንምሳለን፡፡ ለመጭው ትውልድ ነዳጅ ሳይሆን ጉዱጓድ እናወርሳለን” የሚል ነው የሚመስለው፡፡ የዛሬ አስራ አምስት አመት ገደማ ውሃ ማቆር የተባለ ፕሮጀክት ነድፎ ነበር፡፡ እናም ኅብረተሰቡ በየጓሮው ሮቶ ሮቶ የሚያክል ጉድጓድ እየቆፈረ የዝናብ ውሃ እንዲያቁር ትዛዝ ተላልፎለት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ ምንድን ነበር? የየሰፈሩ ሰካራም በየጉድጓዱ እየገባ አለቀ ፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት፤ ስንት ሰካራም አጥንቱን የከሰከሰበትን ፤ ደሙን ያፈሰሰበትን ፕሮጄክት ድንገት ሰረዘ፡፡ በጊዜው የተወሰኑ ሰዎች ለዶማና ላካፋ መግዣ በሚል ወፍራም በጀት አስለቅቀው ከድህነት ተላቀቁ ፡፡ አገሪቱ ግን የግዜር ገበጣ መጫወቻ መስላ ቀጠለች፡፡ የውሃ ማቆር ፕሮጀክሩ ቢቀጥል ኖሮ ዛሬ የህዳሴውን ገደል ለመሙላት ግብጽን አንለማመጥም ነበር፡፡ 

መንግስት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የማይፈጽመውን እያቀደ፤ አዲስአበቤም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በችግሩ እየቀለደ፤ ሃያ አምስት አመት ተገባደደ፡ ፡በውቄም ስኮላርሺፕ በሚል ሰበብ፤ ማንነታቸው ያልታወቀ ፌዴራል ፖሊሶች የሚወረውሩት ቦምብ ወደማይደርስበት ቦታ ተሰደደ፡፡ በግንቦት ወር ወደ አገሩ ሲመለስ ችግር ይገጠመው ይሆን?ወይስ በእጃችን እንይጠፋብን ብለው ይተውት ይሆን? ቀጣዩን ክፍል በመጭው ግንቦት ይጠብቁ፡፡ግን መንግስትን መተቸት ህገመንግሥታዊ መብቴ መሆኑ ይሰመርበት ፡፡ በርግጥ ህገመንግስቱ እንደ ኣዲስ ኣበባ ምግብ ቤቶች Menu ነው፡፡ የተጻፈውን በተግባር ስትፈልገው አታገኘውም፡፡ 
በነገራችን ላይ ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሆነ መጽሄት ላይ “ያመቱ ሰው” ተብለው መሸለማቸውን ሰምቼ ተደስቻለሁ፤ ሲያንሳቸው ነው፡፡ ይሄን ያክል እየተተረበ፤ ይሄን ያክል እየተሰደበ፤ ይሄን ያክል ከታችም ከላይም ንቀት እየተከናነበ ቆሞ መሄድ የቻለ ሰው፤ ሽልማት አነሰው?
እኔም እንሆ፤ ሰሜን አሜሪካ ጫፍ አርፌ 
በጀርባየ የካናዳን የጉም ግድግዳ ተደግፌ 
ከጢሜ ላይ የኮካኮላ ጤዛ ፤ከኪቦርዴ ላይ በረዶየን አራግፌ
“የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ተባብረህ ተነስተህ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ አምባገነኑን ሥርአት ገርስስ” እያልሁ ነጋሪት ስደልቅ ፤አዲስ አበቤም “ወይ ኦን ላይን ያለ ሰው!” እያለ በኔ ላይ ሲስቅ፤ ጀምበር ”ሎግ አውት” አድርጋ ጥልቅ፡፡

ባለፈው 53 የፖለቲካና የሃይማኖት ድርጅቶች መግለጫ አውጡ ሲባል ስቄ ልሞት፡፡ ያሁላ ፓርቲ ቢሮ አለው? ወይስ ህልሙን ባሮጌ ሳምሶናዊት ሸክፎ የሚዞረው ሁሉ ተቆጥሮ ነው?ግሩም ነው መቸም፡፡ ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት አንደኛ ሆና ወተት ይርባታል ፤ አምሳ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲ ኖሯት ፖለቲካው ቸግራታል፤ እንዲያው ምን ይሻላታል?
ድሮ የኔ ቢጤ ባይተዋር ሰው ሲጨንቀው ሰላም ፍለጋ ወደ ቸርች ነበር የሚሄደው፡፡ አሁን በየቤተክስያኑ ድብድብ ነው፡፡ እዚያ ዲሲ ቤተክስያን ልትስሚ ከሄድሽ በነጠላሽ ላይ የጥይት መከላከያ መደረብ አለብሽ ፡፡ እነ አባባ ቆባቸው በሮ እስኪሄድ ሲከታከቱ ታዝበሽ፤ ከተወረወረ መቋሚያ በመትረፍሽ ኣንድየን አመስግነሽ፤ ወደ ቤትሽ ትመለሻለሽ፡፡ ባገር ቤት፤ ቤተክርስትያን ውስጥ አንድ ቄስ በዲያቆናት ሲታጀብ፤ የዲሲ አበሻ ቄሶች ግን በፖሊስ ታጅበው ነው የሚቀድሱ፡፡ እንዲያውም የፈረንጅ ፖሊሶች ለግልግል እየተጠሩ ቤተክስያኑን ከማዘውተራቸው የተነሣ ቅዳሴውን ለምደው ተሰጥኦ ሁሉ መቀበል ጀምረዋል፡፡
በነገራችን ላይ ላገራችን የገጠር ቄስ ክብር አለኝ፡፡ “ዳዋ ጥሶ፤ ጤዛ ልሶ፤ ድንጋይ ተንተርሶ፤ ግርማ ሌሊትን፤ ጸብአ አጋንንትን ታግሶ ፤የሚኖር ነው፡፡ የዲሲ ቄስ በበኩሉ ሙዳየ ምጽዋት አፍሶ፤ አይስክሬሙን ልሶ ፤የንስሃ ልጁን ጡት ተንተርሶ ፤ በቴስታ ተከሳክሶ ይኖራል የሚል ሀሜት አለ፡፡

የዛሬውን የህትመት ዳሰሳየን የምቋጨው በመሬት “ ትንታኔ“ ነው፡፡ ያዲስ አበባ የመሬት ችግር የመነጨው ከዘጠና ሰባት በኋላ ይመስለኛል፡፡ ጌቶች በነዋሪው ተስፋ ስለቆረጡ፤ በስልጣናቸውም ዋስትና ስላጡ፤ “ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅህ” የሚለውን ዘፈን ማንጎራጎር መረጡ፡፡ ይህንን ዝንባሌ እኔና ቢጤዎቼ የቀኝ አዝማች ሰውነቴ “ ሲንድረም ”ብለን እንጠራዋለን፡፡ 

ቀኛማች ሰውነቴ ከደብረማርቆስ ባላባቶች አንዱ ነበሩ፡፡ እና በስድሳ ስድስቱ አብዮት ዋዜማ የጭሰኞቻቸውን መሬት ጆሮ ጆሮውን ብለው ካቲካላ ጠጡበት ፡፡ባላባት ጓደኞቻቸው ለምን እንዲያ እንደሚያረጉ ሲጠይቋቸው“ መሬት ሳትበላኝ ልብላት ብየ ነው” አሉ ይባላል፡፡
ትንታኔውም ይቀጥላል፡፡

ሰበር ዜና ትኩስ ዜና

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በደህነቶች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆን ታማኝ ምንጮች ገልፀውልናል።ምክንያቱም ባለፈው በአባይ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን ያደረጉት ስምምነትን ተግባራዊ ሚሆን ከሆነ የግድቡ ንጣፍ /concrite/ በአከባቢው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ስለሚሰነጣጠቅ ውሃ የመያዝ አቅም አይኖረውም ይህም ማለት ወደ ግድቡ ውሃ በቶሎ እንዲገባ ካልተደረገ ሙሉ በሙሉ ጥቅም መስጠት አይችልም ብለው ለመንግስት ማስጠቀቅያ በመስጣቸው ወያኔ ይህ አስደንጋጭ ወሬ ከሕዝብ ዘንድ እንዳይደርስ በመስጋት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ላይ የ24 ሰዓት ክትትል እንዲደረግ የወያኔ ደህንነቶች ትዛዝ አስተላልፏል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሳለፍነው ሳምንት መጀመርያ ከግብፅና ሱዳን ጋር በግድቡ ዙሪያ አዲስ ጥናት ተደርጎ እስከሚጠናቀቅ ለአስራምስት ወራት አንድ ስኒ ውሃ እንኳን ወደ ግድቡ ላለማስገባት መፈራረሟ ይታወሳል፡፡ እባካችሁን ሼር በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ

Friday, January 1, 2016

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኤርትራ ፕረስ 2015 የ አመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት አሸነፉ



ሽልማቱን የሰጠው  የ ኤርትራ ፕረስ ነው። ለ600 000 ሳምንታዊ አንባቢዎቹ መልካም ለ2016  ምኞቱን በመግለጽ ነው ዜናውን ያበሰረው ፕረሱ። የተንደላቀቀ ኖሩውን በመተው የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ አምባ ገነን አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የነፃነት ታጋዮችን በመቀላቀሉ ለሽልማቱ ተመርጧል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ለማምጣት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም ይላል ፕረሱ። በመጫረሻም የመጨረሻውን አማራጭ የትጥቅ ትግል መጀመር ብቸኛው ምርጫ ሆኖ አገኘው። ራስ ወዳድነትን ያሰወገደና ድፍረትን የተላበሰ ውሳኔው የ2015 የ ኤርትራ ፕረስ ምርጥ ሰው እንዲሆን ዋና ምክንያት ሆኗል። በ 1958  በደብረ ዘይት ከተማ የተወለደው ፕሮፌሰር ብርሐኑ ከወጣትነቱ ጀምሮ የነፃነት ታጋይ እንደነበረ ተገልጿል። ሱዳን ሁለት አመት እንደኖረና በአማሪካን አገር ጥገኝነት ዋስትን በማግኘቱ ወደ አሜሪካ መጓዙን ፕሪሱ ገልጿል። የመጀሪያና ድግሪውንና የፍልስፍና ድግሪውን በምጣኔ ሀብት ላይ መስራቱን ይዘግባል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ በቡከኔል ዩኒቨርስቲ ለ3 አመት በመምህርነት አገልግሏል። በ 1989 የተቓቓመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሞያዎች ማህበር መስራች አባል መሆኑንም ፕሬሱ ያትታል። ፕሮፌሰር ብርሐኑ አሜሪካን አገር የተወለደችውንና ይቻላል የሚል አስተሳሰብ ያላትን ዶር ናርዶስን አገባ። በ 2005 ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ  ቅንጅት አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ በማሸነፉ ዶር ብርሐኑ ከንቲባ ሆኖ ተመረጠ። ፕሮፌሰር ብርሀኑ የ አርበኞች ግንቦት ሰባት መሰራች አባል መሆኑ ይታወቃል ሲል የ ኤርትራ ፕረስ አስታወቀ። የ ኤርትራ ፕሪስ ሽልማቱን ይፋ ያደረገው ዴሴምበር 31 2015 ነው።