ስንታየው ቸኮል ከእስር ከተፍታ በኋላ ዛሬ በፌስቡኩ ላይ የፃፍው
ሰላም ለእናተ ይሁን ወዳጆቼ
መቼም በኢትዮጵያ እየኖሩ ጠፍተሀል አይባልም ያጡትን ሰው እስር ቤት ያገኙታል አይደል የሚባለው በቅድሚያ ሳላም ዛሬን ተገፍተው ለቆዘሙት ወገኖቼ መራራውን የችግርን ውጣ ውረድ እየተጋፈጡ በመከራ ውስጥ ሆነው የነገን ብሩህ ተስፋ ለሚያልሙ ጓዶች ሰላምታዬ ባላችሁበት ይድረሳችሁ ሰላም ልጇ በታሰረ ቁጥር አርባ አራቱን ታቦት እየዞረች ለምታለቅሰው መከረኛዋ እናቴ ሁሌም አስባታለሁ ሰላም አንደበቷ ለሚያስለቅሰው ህፃን ልጄ ፍኖተ ስንታየሁ እና ምህራፍ እግዚያብሄር ይጠብቃችሁ ::
ችግሮቼን የምትጋሪው ባለቤቴ ታላቅ ምስጋና አለኝ በባርነት ውስጥ ተገፍቶ ለሚገኘው ህዝባችን ስንል በምንከፍለው መሰዋትነት ጥልቅ ስሜት ለተሰማችሁ በውጪም በውስጥም ላላችሁ የትግል አጋሮቼ ሀገር ወዳድ ዘመዶቼ ላደረጋችሁት መልካም የትግል አጋርነት የተሰማኝን ስሜት ስገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
መቼም ቢሆን እንደዚህ ለሚሆንልን ህዝባችን የቱንም ያህል የሚያስከፍለውን ብንከፍልም ነገ በታሪክ ፊት የምናወራርደው ሂሳብ ስለሆነ አይቆጨንም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ህዝባችን ከጎናችን እንዳለ አረጋግጠናል በፍጹም ተገፍተን አንቀርም ጥቂት ቡድኖች በሰፈር ተደራጅተው ተፈጥሮ ያደለንን መሬታችንን ቀምተው በአሰቃቂ ርሀባችን ላይ ዳንኪራ የሚጨፍሩብንን ገዢዎች እያየን የነሱ ገበታ ተመልካች ሆነን አንቀርም::
ድህነታችን ፈጣሪ የሰጠን ጸጋ ሳይሆን በዘር የተለከፉ ክፉዎች የሚያዞሩብን አዙሪት ለስደት እየዳረገን የምንሞትበት ታሪክ ተሸክመን አንቀርም አንዳንድ ወዳጆቻችን ቅን ከማሰብ እንደሆነ ቢገባገኝም ልጆችህን አሳድግ አትበሉን እስክንድር ልጁን አቅፎ ማሳደግ አቅቶት አይደለም ::
ሁሉም የነጻነት ታጋይ ይሄ ጠፍቶን አይደለም ነገ የተሸለ ጊዜ ለማድረግ ዛሬ ዋጋ መክፈል አማራጭ የሌለው ምርጫ ስላደረጉብን ነው ልጆቻችን ቦርቀው የሚያድጉበትን የነጻነት ሀገር ፈጥሮ ማለፍ በምድርም በሰማይም ጽድቅ እንጂ ኩነኔ አይደለም::
ተስፋ አለኝ እየመጣ ያለው ወጣት ተራራውን ያፈርሰዋል አታስቡ ሁሉንም ማድረግ ይችላል እየተገፋ ካልወደቀ እየገፋ የሚመጣ ሀይል ተፈጥሯል ልብ ያለው ወደ ልቦናው ተመልሶ ያስብ::
ፈጣሪ እያለቀሰ ያለውን ህዝብ ይመለከታል /////////
No comments:
Post a Comment