እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ የህዝቡ ድምጽ በቀን ብርሀን በአደባባይ ተዘርፏል በሚል ምክንያት ሰላማዊ ዜጎች ተቃውሟቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስታወቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣቸው ብቻ አሁን በህይወት የሌለው እና በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያለው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን (ዘ-ህወሀት) ስብስብ እያልኩ የምጠራው የማፊያ እና ወንጀለኛ ድርጅት መሪ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እልቂት እንዲፈጸም አግዓዚ ለሚባለው ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ቀጥተኛ የሆነ የግል ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች እንዲያልቁ አደረገ፡፡
አጠቃላይ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫው ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ እ.ኤ.አ ግንቦት 16/2005 መለስ ዜናዊ ሁሉንም የፖሊስ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይል አዛዥነቱን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ በህዝብ ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳይካሄድ በማለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የሀገሪቱን መናገሻ ከተማ የፖሊስ እና ልዩ ኃይሉን በማሰማራት የጦር ቀጣና አውድማ አደረጋት፡፡
በቀጣዮቹ ሳምንታት እና ወራት አምባገነኑ እና አረመኔው መለስ በእርሱ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ በሚያሳዬው ማንኛውም ዜጋ ላይ የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሉ ነጻ እርምጃ እንዲወስድ በግሉ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
እ.ኤ.አ በግንቦት እና በህዳር 2005 በጨካኙ መለስ የእልቂት ትዕዛዝ ግድያ የተፈጸመባቸው ንጹሀን ዜጎች ቁጥር ቁጥራቸውን አሳንሰው በሚያቀርቡት የመንግስት ባለስልጣኖች እና እራሱ መለስ ባቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በቀረበው ዘገባ እንኳ 193 ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች 763 የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ (ትክክለኛው የሟቾች እና የቁስለኞች ቁጥር ግን አጣሪ ኮሚሽኑ ካቀረበው ዘገባም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
እነዚያ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች የመለስን በሸፍጥ የተካሄደ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በመቃወም መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም በመሞከራቸው ምክንያት ብቻ እንደ አውሬ እየታደኑ በየመንገዱ እና በየቤቶቻቸው ውስጥ በግፍ ተገድለዋል፡፡እነዚያ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰማዕት ሆነው አልፈዋል፡፡ እ.ኤ.አ ህዳር 13/2005 ከISIL ጋር አንድ ዓይነት የሆነው ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድን በፓሪስ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን እልቂት ፈጽሟል፡፡ ISIL ንጹሀን የፈረንሳይ ዜጎችን እና የሌሎች በፓሪስ ውስጥ ከሚገኙት የ15 ሀገሮች ዜጎችን በመፍጀት እስልምናን እጠብቃሁ ብሏል፡፡
የሸክስፒርን አባባል በመዋስ “ሰይጣን ለእራሱ እኩይ ምግባር ሲል ከመጽሀፍ ቅዱስ (ከቁራን) ይጠቅሳል“ ብለዋል፡፡
አልበርት አነስታይን በአንደ ወቅት እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፣ “ዓለም ሰይጣናዊ ሰዎች በመኖራቸው ምክንያት ብቻ አይደለም ለመኖር አስቸጋሪ የሆነች ቦታ የሆነችው፡፡ ሆኖም ግን ስለዚህ ሰይጣናዊ ሁኔታ ምንም ነገር ሳያደርጉ ዝም ብለው በሚመለከቱ ሰዎች ምክንያት እንጅ፡፡”እኔም እንደዚሁ ኢትዮጵያ ሰይጣናዊ ገዥዎች በመኖራቸው ምክንያት አይለደም ለመኖር አስቸጋሪ ሀገር የሆነችው፣ ሆኖም ግን ስለዚህ ሰይጣናዊ ድርጊት በሀገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ዲያስፖራው ምንም ዓይነት ነገር ባለማድረጋቸው ምክንያት እንጅ እላለሁ ብለዋል ፕሮፌሰሩ፡፡
No comments:
Post a Comment