በደም የተገነባ፣ በደም የተለወሰ፣ በደም የሚያበራ፣ በደም የሚታደስ፣ ደም ግብሩ የሆነ ቀን ሲከበር
የሚከፋችሁ ለምንድን ነው? ደም፣ ደም፣ ደም..... "ያለምንም ደም፣ ኢትዮጰያ ትቅደም" ተብሎ ተጀምሮ
በደም ተቋጨ። "ካሁን በኋላ ጠላታችን ድህነት ብቻ ነው፣ ሰላማችንን የሚነካው የለም" በሚል ስብከት
ተጀምሮ ይኽው አሁን ድረስ ደም እየተገበረ ነው። አሁን ባለው አያያዝ የግንቦት 20 ወዳጆች ደም
የሚጠግቡ አይመስልም፣ገና ብዙ ደም ለማፍሰስ የተዘጋጁ ይመስላል። ክብር ለተስፈነጠሩት ባለ "ራዕዩ"
መሪ!!
በዚህ ቀን ዋዜማ ይህንን ጽሁፍ ሳዘጋጅ "የጫካውን ዘመን ሳናስብ 25 ዓመት ለመማር አይበቃም? "ብዬ
ራሴን ጠይቄ ነበር። ተማር ያለው ከሌሎች ሲማር፣ የግንቦት 20 ባለቤቶች ለምን ለመማር ፈቃደኛ
አይሆኑም? ከቶውንም ሊገባኝ የማይችል