Tuesday, March 15, 2016

ቃለ መጠየቅ ከጋዜጠኛና መምህርት ሪዮት ዓለሙ ጋር 05-02-2016

ከጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ

ጋዜጠኛነዎት ወይንስ የዲሞክራሲ ታጋይ?
ብርቱካን መዴክሳ ሞዴልዎት ናቸው?
ለዲሞክራሲ ግንባታ ለሚደረገው ጥረት ከሴቶች ምን ይጠበቃል?
አረቡ አብዮት ስኬተማ የሆነችው አገር ቱኒዚያ ናት
ለስኬት ያበቃት ደግሞ የሰላም ኖብል ሽልማት ተሻላሚ የሆነው
አወያይ ቡድን ነው ኢትዮጵያ ከቱኒዚያ ምን ትማራለች?


የሚሉት ይገኙበታል 

Wednesday, March 9, 2016

መንግስት በኢትዮጵያ ስለ አለው መረጋጋት የሰጠው መግለጫ ሀሰት ነው



ስልጣናቸውን በቅርብ በለቀቁት የኖርዌይ የመንግሰት ሴክሬታሪ  በኩል የተሰጠው ኢትዮጵያ ውስጥ አስተማማኝ ሰላም አለ የሚለው መግለጫ ሀሳት ነው ሲሉ ጥር አስራ ሁለት የተባለው ለስደተኞች የቆመ ድርጅት ቃል አቀባይ ካርል ኤልዳር ኤቫንግ ለ አፍተን ፖስተን አሳወቁ።  በ አሁኑ ወቅት በተከታታይ በፌስ ቡክ አድራሻዬ የሚደረሱኝ በ ኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በልጆችና ተማሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ አሰቃቂ ናቸው ብለዋል ቃል አቀባዩ። የኖርዌይ መንግስት ሴክሪታሪ የነበሩትንና በቅርብ ስልጣናቸውን የለቀቁትን የዮራን ካልሚርን ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቲወድሮስ አዳሃኖም ጋር ፈገግ ብለው የተነሱትን ፎቶ ከግድግዳዬ ላይ ለጥፌዋለሁ። የኖርዌይ መንግስት በድህረ ገፁ ፌብሪዋሪ 9 ዮራን ካልሚር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በሁ አላ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እድገትም በሰላምም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ መገኘቷን አረጋግጠናል ሲል ፅፏል። ይሁን እንጂ ዮን ካልሚርም ሆነ ቲወድሮስ አዳሀኖም የሰጡት መግለጫ ውሸት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ሳይሆን የፖለቲካ ቀውስ ነው ያለው። ከህዳር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ተካታታይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ይካሄዳሉ  መንግስትም በጥይት ሰዎችን በመግደልና በጅምላ በማሰር ተጠምዷል። የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን የሰባዊ መብት ጥሰት አልተመለከተም። መንግስት ፍላጎቱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከአገር ማስወጣት ብቻ ነው። የጥር 12 ማህበር ቃል አቀባይ ካርል ኤልዳር ኤቫንግ ሪፖርቱን በኖርዌይ ታዋቂ ለሆነው አፍተን ፖስተን ጋዜጣ የሰጡት ማርች 3. 2016 ነው።

Weekly News

ኢትዮ ኖርዌይ ቲቪና ራዲዮ ለኖርዌይ ፍትህ ሚኒስቴር 8 ጥያቄዎችን አቀረበ
መንግስት በኢትዮጵያ ስለ አለው መረጋጋት የሰጠው መግለጫ ሀሰት ነው